ኢሳይያስ 60:12-16 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

12. ለአንቺ የማይገዛ ሕዝብና መንግሥት ይጠፋል፤ፈጽሞም ይደመሰሳል።

13. የመቅደሴን ቦታ ለማስጌጥ፣የሊባኖስ ክብር፣ጥዱ፣ አስታውና ባርሰነቱ በአንድነት ወደ አንቺ ይመጣሉ፤እግሬ የሚያርፍበትንም ስፍራ አከብራለሁ።

14. የአስጨናቂዎችሽ ወንዶች ልጆች እየሰገዱ ወደ አንቺ ይመጣሉ፤የናቁሽም ሁሉ እግርሽ ላይ ይደፋሉ፤ የእግዚአብሔር ከተማ፣የእስራኤል ቅዱስ ገንዘብ የሆንሽው ጽዮን ብለው ይጠሩሻል።

15. “የተተውሽና የተጠላሽ፣ማንም ሰው የማያልፍብሽ ብትሆኝም እንኳ፣እኔ የዘላለም ትምክሕት፣የትውልድም ሁሉ ደስታ አደርግሻለሁ።

16. የመንግሥታትን ወተት ትጠጫለሽ፤የነገሥታትንም ጡት ትጠቢያለሽ፤ከዚያም እኔ እግዚአብሔር አዳኝሽ፣ቤዛሽም እኔ የያዕቆብ ኀያል እንደሆንሁ ታውቂያለሽ።

ኢሳይያስ 60