ኢሳይያስ 53:3-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. በሰዎች የተናቀና የተጠላ፣የሕማም ሰውና ሥቃይ ያልተለየው ነበር።ሰዎች ፊታቸውን እንደሚያዞሩበት ዐይነት፣የተናቀ ነበር፤ እኛም አላከበርነውም።

4. በርግጥ እርሱ ደዌያችንን ወሰደ፤ሕመማችንንም ተሸከመ፤እኛ ግን በእግዚአብሔር እንደ ተመታ፣እንደ ተቀሠፈ፣ እንደ ተሠቃየም ቈጠርነው።

5. ነገር ግን እርሱ ስለ መተላለፋችን ተወጋ፤ስለ በደላችንም ደቀቀ፤በእርሱ ላይ የወደቀው ቅጣት ለእኛ ሰላም አመጣልን፤በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።

6. እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን፤እያንዳንዳችንም በየመንገዳችን ነጐድን፤ እግዚአብሔርም፣ የሁላችንን በደልበእርሱ ላይ ጫነው።

7. ተጨነቀ፤ ተሠቃየም፤ነገር ግን አፉን አልከፈተም፤እንደ ጠቦትም ለዕርድ ተነዳ፤በሸላቾች ፊት ዝም እንደሚል በግ፣አፉን አልከፈተም።

8. በማስጨነቅና በፍርድ ተወሰደ፤ስለ ሕዝቤ ኀጢአት ተመቶ፣ከሕያዋን ምድር እንደ ተወገደ፣ከትውልዱ ማን አስተዋለ?

ኢሳይያስ 53