ኢሳይያስ 5:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ስለ ወዳጄ፣ደግሞም ስለ ወይን ቦታው ልዘምር፤ወዳጄ በለምለም ኰረብታ ላይየወይን ቦታ ነበረው።

2. መሬቱን ቈፈረ፤ ድንጋይንም ለቅሞ አወጣ፤ምርጥ የሆነውንም ወይን ተከለበት።በመካከሉ መጠበቂያ ማማ ሠራ፤የወይን መጭመቂያ ጒድጓድም አበጀ፤ከዚያ መልካም ፍሬ ያፈራል ብሎ አሰበ፤ነገር ግን ኮምጣጣ ፍሬ አፈራ።

3. “እናንት በኢየሩሳሌም የምትኖሩና የይሁዳ ሰዎች ሆይ፤በእኔና በወይኔ ቦታ መካከል እስቲ ፍረዱ።

ኢሳይያስ 5