6. እነዚህን ነገሮች ሰምተሃል፤ ሁሉንም ተመልከታቸው፤ራስህ ትክክለኛነታቸውን አትመሰክርምን?“ከአሁን ጀምሮ አዳዲስ ነገሮችን፣የተሰወሩብህን ያላወቅሃቸውን ነገሮች እነግርሃለሁ።
7. እነርሱም የተፈጠሩት አሁን እንጂ ጥንት አይደለም፤ስለ እነርሱም ከዛሬ በፊት አልሰማህም።ስለዚህ፣ ‘አዎን፤ ስለ እነርሱ ዐውቃለሁ’ማለት አትችልም።
8. አልሰማህም ወይም አላውቅህም፤ጆሮህ ከጥንት የተከፈተ አልነበረም፤አንተ አታላይ እንደ ነበርህ፣ከልጅነትህ ጀምሮ ዐመፀኛ መባልህን ዐውቄአለሁና።
9. ስለ ስሜ ስል ቍጣዬን አዘገያለሁ፤ስለ ምስጋናዬም ስል ከአንተ እገታዋለሁ፤ይኸውም እንዳልቈርጥህ ነው።
10. እነሆ፤ እንደ ብር ባይሆንም አንጥሬሃለሁ፤በመከራ እቶን ፈትኜሃለሁ።
11. ስለ ራሴ፣ ስለ ራሴ ስል አደርጋለሁ፤ራሴን ለውርደት እንዴት አሳልፌ እሰጣለሁ?ክብሬን ለማንም አልሰጥም።
12. “ያዕቆብ ሆይ፤የጠራሁህ እስራኤል ሆይ፤ ስማኝ፤እኔ እኔው ነኝ፤ፊተኛው እኔ ነኝ፤ ኋለኛውም እኔ ነኝ።
13. ምድርን የመሠረተች የእኔው እጅ ናት፤ሰማያትን የዘረጋችም ቀኝ እጄ ናት፤በምጠራቸው ጊዜ፣ሁሉም በአንድነት ይቆማሉ።