ኢሳይያስ 47:3-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. ዕርቃንሽ ይገለጥ፤ኀፍረትሽ ይታይ፤እበቀላለሁ፤እኔ ማንንም አልተውም።

4. የሚቤዠን የእስራኤል ቅዱስ፣ስሙ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው።

5. “አንቺ የባቢሎናውያን ልጅ ሆይ፤ወደ ጨለማ ግቢ፤ ዝም ብለሽም ተቀመጪ፤ከእንግዲህ የመንግሥታት እመቤት፣ተብለሽ አትጠሪም።

6. ሕዝቤን ተቈጥቼ ነበር፤ርስቴን አርክሼው ነበር፤አሳልፌ በእጅሽ ሰጠኋቸው፤አንቺ ግን አልራራሽላቸውም፤በዕድሜ በገፉት ላይ እንኳ፣እጅግ ከባድ ቀንበር ጫንሽባቸው።

ኢሳይያስ 47