1. “አንቺ የባቢሎን ድንግል ልጅ ሆይ፤ውረጂ፤ በትቢያ ላይ ተቀመጪ፤አንቺ የባቢሎናውያን ልጅ ሆይ፤ከዙፋንሽ ውረጂ፤ መሬት ላይ ተቀመጪ፤ከእንግዲህ ውብ ወይም ለግላጋ፣ተብለሽ አትጠሪም።
2. ወፍጮ ወስደሽ እህል ፍጪ፤መሸፋፈኛሽን አውልቂ፤ቀሚስሽንም ከፍ ከፍ አድርጊ፤ ባትሽን ግለጪ፤እየተንገዳገድሽ ወንዙን ተሻገሪ።
3. ዕርቃንሽ ይገለጥ፤ኀፍረትሽ ይታይ፤እበቀላለሁ፤እኔ ማንንም አልተውም።
4. የሚቤዠን የእስራኤል ቅዱስ፣ስሙ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው።