ኢሳይያስ 44:21-24 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

21. “እስራኤል ሆይ፤ ባሪያዬ ነህና፣ያዕቆብ ሆይ፤ ይህን አስብ።እኔ ሠርቼሃለሁ፤ አንተም ባሪያዬ ነህ፤እስራኤል ሆይ፤ አልረሳህም።

22. መተላለፍህን እንደ ደመና፣ኀጢአትህን እንደ ማለዳ ጭጋግ ጠርጌ አስወግጃለሁ፤ተቤዥቼሃለሁናወደ እኔ ተመለስ።”

23. ሰማያት ሆይ፤ እግዚአብሔር ይህን አድርጎአልና ዘምሩ፤የምድር ጥልቆች ሆይ፤ በደስታ ጩኹ።እናንት ተራሮች፣እናንት ደኖችና ዛፎቻችሁ ሁሉ እልል በሉ፤ እግዚአብሔር ያዕቆብን ተቤዥቶአል፣በእስራኤልም ክብሩን ገልጦአልና።

24. “ከማሕፀን የሠራህ፣ የተቤዠህም፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ሁሉን ነገር የፈጠርሁ፣ብቻዬን ሰማያትን የዘረጋሁ፣ምድርን ያንጣለልሁ፣እኔ እግዚአብሔር ነኝ።

ኢሳይያስ 44