14. የእስራኤል ቅዱስ፣የሚቤዣችሁ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ስለ እናንተ በባቢሎን ላይ ሰራዊት እሰዳለሁ፤በሚመኩባቸውም መርከቦች፣ባቢሎናውያንን ሁሉ እንደ ኰብላይ አመጣለሁ።
15. እኔ እግዚአብሔር፣ የእናንተ ቅዱስ፣የእስራኤል ፈጣሪ፣ ንጉሣችሁ ነኝ።”
16. በባሕር ውስጥ መንገድ፣በማዕበል ውስጥ መተላለፊያ ያበጀ፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤
17. እንደ ገና ላይነሡ እዚያው እንዲተኙ፣እንደ ጧፍ ኵስታሪ ረግፈው እንዲጠፉ፣ሠረገሎችንና ፈረሶችን፣ሰራዊቱንና ደጀኑን በአንድነት ያወጣ እንዲህ ይላል፤