ኢሳይያስ 42:13-15 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

13. እግዚአብሔር እንደ ኀያል ሰው ይዘምታል፤እንደ ተዋጊ በወኔ ይነሣል፤የቀረርቶ ጩኸት ያሰማል፤ጠላቶቹንም ድል ያደርጋል።

14. “ለረጅም ጊዜ ዝም አልሁ፤ጸጥ አልሁ፤ ራሴንም ገታሁ፤አሁን ግን ምጥ እንደ ያዛት ሴት፣እጮኻለሁ፤ ቁና ቁና እቃትታለሁ፤ እተነፍሳለሁ።

15. ተራራውንና ኰረብታውን አፈርሳለሁ፤ዕፀዋቱን ሁሉ አደርቃለሁ፤ወንዙንም ደሴት አደርጋለሁ፤ኵሬውን አደርቃለሁ።

ኢሳይያስ 42