ኢሳይያስ 41:8-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

8. “አንተ ግን፣ ባሪያዬ እስራኤል፣የመረጥሁ ያዕቆብ፣የወዳጄ የአብርሃም ዘር ሆይ፤

9. ከምድር ዳርቻ ያመጣሁህ፣ከአጥናፍም የጠራሁህ፣‘አንተ ባሪያዬ ነህ’ ያልሁህ፤መረጥሁህ እንጂ፤ አልጣልሁህም።

10. እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤አምላክህ ነኝና አትደንግጥ።አበረታሃለሁ፤ እረዳሃለሁ፤በጽድቄም ቀኝ እጄ ደግፌ እይዝሃለሁ።

11. “እነሆ፤ የተቈጡህ ሁሉ፣እጅግ ያፍራሉ፤ ይዋረዳሉም፤የሚቋቋሙህ፣እንዳልነበሩ ይሆናሉ፤ ይጠፋሉም።

ኢሳይያስ 41