ኢሳይያስ 35:7-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

7. ንዳዳማው ምድር ኵሬ ይሆናል፤የተጠማው መሬት ውሃ ያመነጫል።ቀበሮዎች በተኙባቸው ጒድጓዶች፣ሣር፣ ሸምበቆና ደንገል ይበቅልበታል።

8. በዚያ አውራ ጐዳና ይሆናል፤“የተቀደሰ መንገድ” ተብሎ ይጠራል።የረከሱ አይሄዱበትም፤በመንገዱ ላይ ላሉት ብቻ ይሆናል።ገራገሮችም ከመንገዱ አይስቱም።

9. አንበሳ አይኖርበትም፤ነጣቂ አውሬም አይወጣበትም፤እነዚህማ በዚያ ስፍራ አይገኙም፤የዳኑት ብቻ በዚያ ይሄዳሉ፤

ኢሳይያስ 35