ኢሳይያስ 33:22-24 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

22. እግዚአብሔር ዳኛችን ነው፤ እግዚአብሔር ሕግ ሰጪያችን ነው፤ እግዚአብሔር ንጉሣችን ነው፤የሚያድነንም እርሱ ነውና።

23. መወጠሪያ ገመድህ ላልቶአል፤ምሰሶው ጠብቆ አልተተከለም፤ሸራው አልተወጠረም፤በዚያ ጊዜ ታላቅ ምርኮ ይከፋፈላል፤አንካሳ እንኳ ሳይቀር ምርኮ ይወስዳል።

24. በጽዮን ተቀምጦ፣ “ታምሜአለሁ” የሚል አይኖርም፤በዚያ የሚኖሩ ሰዎች ኀጢአትም ይቅር ይባላል።

ኢሳይያስ 33