ኢሳይያስ 33:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. አንተ ሳትጠፋ የምታጠፋ፣አንት አጥፊ፣ ወዮልህ!አንተ ሳትካድ የምትክድ፣አንት ከዳተኛ፣ ወዮልህ!ማጥፋትን በተውህ ጊዜ፣ትጠፋለህ፤ክሕደትህንም በተውህ ጊዜ ትከዳለህ።

2. እግዚአብሔር ሆይ፤ ማረን፤አንተን ተስፋ አድርገናል።በየማለዳው ብርታት፣በጭንቅ ጊዜም ድነት ሁነን።

3. ሕዝቦች በድምፅህ ነጐድጓድ ይሸሻሉ፣መንግሥታት ስትነሣ ይበተናሉ።

ኢሳይያስ 33