ኢሳይያስ 29:10-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

10. እግዚአብሔር ከባድ እንቅልፍ ጥሎባችኋል፤ዐይኖቻችሁን፣ ነቢያትን ጨፍኖባችኋል፤ራሶቻችሁን፣ ባለ ራእዮችን ሸፍኖባችኋል።

11. ይህ ሁሉ ራእይ በጥቅልል መጽሐፍ ውስጥ እንደ ታሸገ ቃል ሆኖባችኋል። ጥቅልሉንም መጽሐፍ ማንበብ ለሚችል ሰው፣ “እባክህ አንብልን” ብላችሁ ብትሰጡት፣ “ታሽጓልና አልችልም” ይላችኋል።

12. ደግሞም ጥቅልሉን መጽሐፍ ማንበብ ለማይችል ሰው፣ “እባክህን አንብልን” ብላችሁ ብትሰጡ፣ “ማንበብ አልችልም” ይላችኋል።

13. እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ይህ ሕዝብ በአፉ ወደ እኔ ይቀርባል፤በከንፈሩም ያከብረኛል፤ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነው፤የሚያመልከኝም፣ሰው ባስተማረው ሰው ሠራሽ ሥርዐት ብቻ ነው።

ኢሳይያስ 29