ኢሳይያስ 28:2-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

2. እነሆ፤ ጌታ ኀያልና ብርቱ የሆነ ነገር አለው፤ይህም እንደ በረዶ ወጀብ፣ እንደሚያጠፋ ዐውሎ ነፋስ፣እንደ ኀይለኛ ማዕበል፣ እንደ ከባድ ዝናብ፣በኀይል ወደ ምድር ይጥላታል።

3. የኤፍሬም ሰካራሞች የመታበያ አክሊል፣በእግር ይረገጣል።

4. በለምለሙ ሸለቆ ዐናት ላይ ጒብ ብላ፣የክብሩ ውበት የሆነች ጠውላጋ አበባ፣ከመከር በፊት እንደ ደረሰች፣ሰውም ድንገት አይቶ እንደሚቀጥፋትወዲያውኑም እንደሚውጣት በለስ ትሆናለች።

5. በዚያን ቀን የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ለተረፈው ሕዝቡ፣የክብር ዘውድ፣የውበትም አክሊል ይሆናል።

ኢሳይያስ 28