1. ለኤፍሬም ሰካራሞች የመታበያ አክሊል ለሆነች፣በለመለመ ሸለቆ ዐናት ላይ ጒብ ብላ፣የክብሩ ውበት ለሆነች ጠውላጋ አበባ፣የወይን ጠጅ ለዘራቸው መኵራሪያ ለሆነች፣ለዚያች ከተማ ወዮላት!
2. እነሆ፤ ጌታ ኀያልና ብርቱ የሆነ ነገር አለው፤ይህም እንደ በረዶ ወጀብ፣ እንደሚያጠፋ ዐውሎ ነፋስ፣እንደ ኀይለኛ ማዕበል፣ እንደ ከባድ ዝናብ፣በኀይል ወደ ምድር ይጥላታል።
3. የኤፍሬም ሰካራሞች የመታበያ አክሊል፣በእግር ይረገጣል።