ኢሳይያስ 26:7-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

7. የጻድቃን መንገድ ቅን ናት፤አንተ ቅን የሆንህ ሆይ፤የጻድቃንን መንገድ ታቃናለህ።

8. እግዚአብሔር ሆይ፤ በሕግህ ጐዳና በመሄድ፣አንተን ተስፋ አድርገናል፤ስምህና ዝናህ፣የልባችን ምኞት ነው።

9. ነፍሴ በሌሊት ትናፍቅሃለች፤መንፈሴም በውስጤ ትፈልግሃለች።ፍርድህ ወደ ምድር በመጣ ጊዜ፣የዓለም ሕዝቦች ጽድቅን ይማራሉ።

10. ክፉዎች ርኅራኄ ቢደረግላቸው እንኳ፣ጽድቅን አይማሩም፤በቅንነት ምድር እንኳ ክፋትን ያደርጋሉ፤ የእግዚአብሔርንም ግርማ አያስተውሉም።

ኢሳይያስ 26