ኢሳይያስ 22:7-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

7. መልካሞቹ ሸለቆዎችሽ በሠረገሎች ተሞልተዋል፤ፈረሰኞችም በከተማዪቱ በሮች ላይ ቆመዋል፤

8. የይሁዳን መከላከያዎች ገልጧል።በዚያን ቀን በዱር ግምጃ ቤት የነበረውን፣የጦር መሣሪያ ተመለከትህ፤

9. የዳዊት ከተማ፣ብዙ ፍርስራሾች እንዳሉበት አያችሁ፤በታችኛውም ኵሬ፣ውሃ አጠራቀማችሁ።

10. በኢየሩሳሌም ያሉትን ቤቶች ቈጠራችሁ፤ቅጥሩን ለመጠገንም ቤቶቹን አፈረሳችሁ።

ኢሳይያስ 22