ኢሳይያስ 21:4-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. ልቤ ተናወጠ፤ፍርሀት አንቀጠቀጠኝ፤የጓጓሁለት ውጋጋን፣ታላቅ ፍርሀት አሳደረብኝ።

5. ማእዱን አሰናዱ፤ምንጣፉን አነጠፉ፤በሉ፤ ጠጡ!እናንት ሹማምት ተነሡ፤ጋሻውን በዘይት ወልውሉ!

6. ጌታ እንዲህ አለኝ፤“ሂድ፤ ጠባቂ አቁም፤ያየውንም ይናገር፤

7. በፈረሶች የሚሳብ፣ሠረገሎችን ሲያይ፣በአህያ ላይ የሚቀመጡትን፣በግመል የሚጋልቡትን ሲመለከት፣ያስተውል፣በጥንቃቄም ያስተውል።”

8. ጠባቂው ጮኸ፤ እንዲህም አለ፤“ጌታ ሆይ፤ በየቀኑ ማማ ላይ ቆሜአለሁ፤በየሌሊቱም በቦታዬ አለሁ።

ኢሳይያስ 21