ኢሳይያስ 16:12-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

12. ሞዓብ ወደ ኰረብታዋ ብትወጣ፣ትርፏ ድካም ብቻ ነው፤ለጸሎት ወደ መቅደሷ ብትገባም፣ዋጋ የለውም።

13. እግዚአብሔር አስቀድሞ ስለ ሞዓብ የተናገረው ቃል ይህ ነው።

14. አሁን ግን እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “የተቀጠረ ሠራተኛ ቀን እንደሚቈጥር፣ የሞዓብ ክብርና የሕዝቧ ብዛት በሦስት ዓመት ውስጥ ይዋረዳል፤ የሚቀረውም ሕዝብ ጥቂትና ደካማ ይሆናል።”

ኢሳይያስ 16