ኢሳይያስ 12:4-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. በዚያን ቀን እንዲህ ትላላችሁ፤“እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ስሙንም ጥሩ፤ያደረገውንም በአሕዛብ መካከል አስታውቁ፤ስሙ ከፍ ከፍ ማለቱንም ዐውጁ።

5. ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ ታላቅ ሥራ ሠርቶአልና፤ይህም ለዓለም ሁሉ ይታወቅ።

6. የጽዮን ሕዝብ ሆይ፤ እልል በሉ፤በደስታም ዘምሩ፤በመካከላችሁ ያለው የእስራኤል ቅዱስ ታላቅ ነውና።

ኢሳይያስ 12