3. እግዚአብሔርን በመፍራት ደስ ይለዋል፤ዐይኑ እንዳየ አይፈርድም፤ጆሮውም እንደ ሰማ አይበይንም።
4. ነገር ግን ለድኾች በጽድቅ ይፈርዳል፤ለምድር ምስኪኖችም ፍትሕን ይበይናል፤በአፉ በትር ምድርን ይመታል፤በከንፈሩም እስትንፋስ ክፉዎችን ይገድላል።
5. ጽድቅ የወገቡ መታጠቂያ፣ታማኝነትም የጐኑ መቀነት ይሆናል።
6. ተኵላ ከበግ ጠቦት ጋር ይኖራል፤ነብርም ከፍየል ግልገል ጋር ይተኛል፤ጥጃ፣ የአንበሳ ደቦልና የሰባ ከብት በአንድነት ይሰማራሉ፤ትንሽ ልጅም ይመራቸዋል።
7. ላምና ድብ በአንድነት ይሰማራሉ፤ልጆቻቸውም አብረው ይተኛሉ፤አንበሳም እንደ በሬ ገለባ ይበላል።