አሞጽ 7:16-17 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

16. እንግዲህ የእግዚአብሔርን ቃል ስማ።አንተ፣ “ ‘በእስራኤል ላይ ትንቢት አትናገር፤በይስሐቅም ቤት ላይ አትስበክ’ ትላለህ።

17. “ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤”‘ሚስትህ በከተማዪቱ ውስጥ ጋለሞታ ትሆናለች፤ወንዶችና ሴቶች ልጆችህም በሰይፍ ይወድቃሉ፤ምድርህም እየተለካ ይከፋፈላል፤አንተ ራስህ በረከሰ ምድር ትሞታለህ፤እስራኤልም ከትውልድ አገሩ፣ተማርኮ ይሄዳል።’ ”

አሞጽ 7