አሞጽ 5:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. የእስራኤል ቤት ሆይ፤ ስለ እናንተ የምደረድረውን ይህን የሙሾ ቃል ስሙ፤

2. “ድንግሊቱ እስራኤል ወደቀች፤ከእንግዲህም አትነሣም፤በገዛ ምድሯ ተጣለች፤የሚያነሣትም የለም።”

3. ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“አንድ ሺህ ብርቱዎችን ለእስራኤል የምታዘምት ከተማ፣አንድ መቶ ብቻ ይቀሯታል፤አንድ መቶ ብርቱዎችን የምታዘምተውም፣ዐሥር ብቻ ይቀሯታል።”

አሞጽ 5