ሰቆቃወ 5:17-20 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

17. ከዚህ የተነሣ ልባችን ደከመ፤ከእነዚህ የተነሣም ዐይናችን ፈዘዘ፤

18. ባዶዋን የቀረችው የጽዮን ተራራ፣የቀበሮዎች መፈንጫ ሆናለችና።

19. አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ለዘላለም ትገዛለህ፤ዙፋንህ ከትውልድ እስከ ትውልድ ይኖራል።

20. ስለ ምን ፈጽመህ ትረሳናለህ?ስለምንስ ለረዥም ጊዜ ትተወናለህ?

ሰቆቃወ 5