ራእይ 8:8-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

8. ሁለተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ ትልቅ ተራራ የሚመስል ነገር በእሳት እየተቀጣጠለ ወደ ባሕር ተጣለ፤ የባሕሩ አንድ ሦስተኛ ወደ ደም ተለወጠ፤

9. በባሕሩም ውስጥ ከሚኖሩት ሕያዋን ፍጡራን አንድ ሦስተኛ ሞተ፤ የመርከቦችም አንድ ሦስተኛ ወደመ።

10. ሦስተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ እንደ ችቦ የሚነድ ታላቅ ኮከብ በወንዞች አንድ ሦስተኛና በውሃ ምንጮች ላይ ከሰማይ ወደቀ፤

11. የኮከቡም ስም “እሬቶ” ይባል ነበር። የውሃውም አንድ ሦስተኛ መራራ ሆነ፤ ውሃው መራራ ከመሆኑ የተነሣም ብዙ ሰዎች ሞቱ።

ራእይ 8