5. ከዚያም በውሆች ላይ ሥልጣን ያለው መልአክ እንዲህ ሲል ሰማሁ፤“ያለህና የነበርህ ቅዱሱ ሆይ፤እንዲህ ስለ ፈረድህ፣አንተ ጻድቅ ነህ፤
6. የቅዱሳንንና የነቢያትን ደም ስላፈሰሱ፣አንተም ደግሞ ደም እንዲጠጡ አደረግሃቸው፤ ይህ የሚገባቸው ነውና።”
7. እንዲሁም ከመሠዊያው እንዲህ የሚል ድምፅ ሰማሁ፤“አዎን፤ ሁሉን ቻይ ጌታ አምላክ ሆይ፤ፍርድህ እውነትና ጽድቅ ነው።”
8. አራተኛውም መልአክ ጽዋውን በፀሓይ ላይ አፈሰሰ፤ ፀሓይም ሰዎችን በእሳት እንድታቃጥል ኀይል ተሰጣት።