ራእይ 12:4-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. ጅራቱ የከዋክብትን አንድ ሦስተኛ ከሰማይ ስቦ ወደ ምድር ጣላቸው፤ እርሷም በወለደች ጊዜ ልጇን ለመዋጥ ፈልጎ ዘንዶው ልትወልድ በተቃረበችው ሴት ፊት ቆመ።

5. ሕዝቦችን ሁሉ በብረት በትር የሚገዛውን ወንድ ልጅ ወለደች፤ ልጇም ወደ እግዚአብሔርና ወደ ዙፋኑ ተነጠቀ።

6. ሴቲቱም አንድ ሺህ ሁለት መቶ ሥልሳ ቀን ክብካቤ እንዲደረግላት እግዚአብሔር ወዳ ዘጋጀላት ስፍራ ወደ በረሓ ሸሸች።

ራእይ 12