1. ልጄ ሆይ፤ ለጎረቤትህ ዋስ ብትሆን፣ስለ ሌላውም ሰው እጅ መትተህ ቃል ብትገባ፣
2. በተናገርኸው ነገር ብትጠመድ፣ከአፍህ በወጣውም ቃል ብትያዝ፣
3. ልጄ ሆይ፤ ራስህን ለማዳን ይህን አድርግ፤በጎረቤትህ እጅ ስለ ወደቅህ፣ሄደህ ራስህን አዋርድ፤ጎረቤትህን አጥብቀህ ነዝንዘው።
4. ዐይኖችህ እንቅልፍ አይያዛቸው፣ሽፋሽፍቶችህም አያንጐላጁ።
5. ከአዳኝ እጅ እንዳመለጠች ሚዳቋ፣ከአጥማጅ ወጥመድ እንዳፈተለከች ወፍ ራስህን አድን።