ምሳሌ 4:6-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. ጥበብን አትተዋት፤ እርሷም ከለላ ትሆንሃለች፤አፍቅራት፤ እርሷም ትጠብቅሃለች።

7. ጥበብ ታላቅ ነገር ናት፤ ስለዚህ ጥበብን አግኛት፤ያለህን ሁሉ ብታስከፍልህም ማስተዋልን ገንዘብህ አድርጋት።

8. ክብርን ስጣት፤ ከፍ ከፍ ታደርግሃለች፤ዕቀፋት፤ ታከብርሃለች፤

9. በራስህ ላይ ሞገሳማ አክሊል ትደፋልሃለች፤የክብር ዘውድም ታበረክትልሃለች።

10. ልጄ ሆይ፤ አድምጠኝ፤ ቃሌንም ልብ በል፤የሕይወት ዘመንህም ትበዛለች።

11. በጥበብ ጐዳና አስተምርሃለሁ፤ቀጥተኛውንም መንገድ አሳይሃለሁ።

ምሳሌ 4