ምሳሌ 31:12-16 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

12. በሕይወት ዘመኗ ሁሉ፣መልካም ታደርግለታለች እንጂ አትጐዳውም።

13. የበግ ጠጒርና የተልባ እግር መርጣ፣ሥራ በሚወዱ እጆቿ ትፈትላቸዋለች።

14. እንደ ንግድ መርከብ፣ምግቧን ከሩቅ ትሰበስባለች።

15. ገና ሳይነጋ ትነሣለች፤ለቤተ ሰቧ ምግብ፣ለሴት አገልጋዮቿም ድርሻቸውን ትሰጣለች።

16. ራሷ አስባ የዕርሻ መሬት ትገዛለች፤በምታገኘውም ገንዘብ ወይን ትተክላለች።

ምሳሌ 31