3. ድኾችን የሚያስጨንቅ ሰው፣ሰብል እንደሚያጠፋ ኀይለኛ ዝናብ ነው።
4. ሕግን የሚተዉ ክፉዎችን ያወድሳሉ፤ሕግን የሚጠብቁ ግን ይቋቋሟቸዋል።
5. ክፉዎች ፍትሕን አያስተውሉም፤ እግዚአብሔርን የሚሹ ግን ሙሉ በሙሉ ያውቁታል።
6. በአካሄዱ ነውር የሌለበት ድኻ፣መንገዱ ጠማማ ከሆነ ባለጠጋ ይሻላል።
7. ሕግን የሚጠብቅ አስተዋይ ልጅ ነው፤ከሆዳሞች ጋር ጓደኛ የሚሆን ግን አባቱን ያዋርዳል።
8. በከፍተኛ ወለድ ሀብቱን የሚያካብት፣ለድኻ ለሚራራ፣ ለሌላው ሰው ያከማችለታል።
9. ሕግን ላለመስማት ጆሮውን የሚደፍን፣ጸሎቱ እንኳ አስጸያፊ ነው።
10. ቅኖችን በክፉ መንገድ የሚመራ፣በቈፈረው ጒድጓድ ይገባል፤ንጹሓን ግን መልካም ነገርን ይወርሳሉ።