ምሳሌ 27:22-26 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

22. ጅልን በሙቀጫ ብትወቅጠው፣እንደ እህልም በዘነዘና ብታደቀው፣ጅልነቱን ልታስወግድለት አትችልም።

23. በጎችህ በምን ሁኔታ እንዳሉ ደህና አድርገህ ዕወቅ፤መንጋህንም ተንከባከብ፤

24. ሀብት ለዘላለም አይኖርምና፤ዘውድም ከትውልድ ወደ ትውልድ ጸንቶ አይኖርም።

25. ደረቁ ሣር ተወግዶ፣ አዲሱ ብቅ ሲል፣በየኰረብታው ላይ ያለው ሣር ተሰብስቦ ሲገባ፣

26. ከበግ ጠቦቶች ልብስ ታገኛለህ፤ፍየሎችም የዕርሻ መሬት መግዣ ይሆኑሃል።

ምሳሌ 27