ምሳሌ 25:25-27 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

25. ከሩቅ የሚመጣ መልካም ዜና፣የተጠማችን ነፍስ እንደሚያረካ ቀዝቃዛ ውሃ ነው።

26. ለክፉ ሰው የሚንበረከክ ጻድቅ፣እንደ ደፈረሰ ምንጭ ወይም እንደ ተበከለ የጒድጓድ ውሃ ነው።

27. ከመጠን በላይ ማር መብላት ጥሩ አይደለም፤የራስንም ክብር መሻት አያስከብርም።

ምሳሌ 25