ምሳሌ 24:15-18 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

15. በጻድቅ ሰው ቤት ላይ እንደ ወንበዴ አታድፍጥ፤መኖሪያውንም በድንገት አታጥቃ፤

16. ጻድቅ ሰባት ጊዜ እንኳ ቢወድቅ ይነሣልና፤ክፉዎች ግን በጥፋት ይወድቃሉ።

17. ጠላትህ ሲወድቅ ደስ አይበልህ፤ሲሰናከልም ልብህ ሐሤት አያድርግ፤

18. አለዚያ እግዚአብሔር ይህን አይቶ ደስ አይለውም፤ቍጣውንም ከእርሱ ይመልሳል።

ምሳሌ 24