ምሳሌ 22:3-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. አስተዋይ ሰው አደጋ ሲያይ መጠጊያ ይሻል፤ብስለት የጐደለው ግን በዚያው ይቀጥላል፤ መከራም ያገኘዋል።

4. ትሕትናና እግዚአብሔርን መፍራት፣ሀብትን፣ ክብርንና ሕይወትን ያስገኛል።

5. በክፉዎች መንገድ ላይ እሾህና ወጥመድ አለ፤ነፍሱን የሚጠብቅ ግን ከእነዚህ ይርቃል።

6. ልጅን የሚሄድበትን መንገድ አስተምረው፤በሚሸመግልበት ጊዜ ከዚያ ፈቀቅ አይልም።

7. ባለጠጋ ድኻን ይገዛል፤ተበዳሪም የአበዳሪ ባሪያ ነው።

ምሳሌ 22