ምሳሌ 22:16-25 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

16. ሀብቱን ለማካበት ድኻን የሚበድል፣ለባለጠጋም ስጦታ የሚያቀርብ፣ ሁለቱም ይደኸያሉ።

17. የጠቢባንን ቃል ልብ ብለህ ስማ፤ልብህም ወደ ትምህርቴ ያዘንብል፤

18. በልብህ ስትጠብቃቸው፣ሁሉም በከንፈሮችህ ላይ የተዘጋጁ ሲሆኑ ደስ ይላልና።

19. ስለዚህ እምነትህ በእግዚአብሔር ላይ እንዲሆን፣ዛሬ አንተን ራስህን አስተምርሃለሁ።

20. የምክርና የዕውቀት ቃል የሆኑ፣መልካም ትምህርቶችን አልጻፍሁልህምን?

21. ለላከህ ተገቢውን መልስ ትሰጥ ዘንድ፣እውነተኛውና የታመኑ ቃሎችን እንዳስተምርህ አይደለምን?

22. ድኾች በመሆናቸው ብቻ ድኾችን አትበዝብዛቸው፤ችግረኛውንም በአደባባይ አታንገላታው፤

23. እግዚአብሔር ይፋረድላቸዋልና፤የሚቀሟቸውንም ይቀማቸዋል።

24. ከግልፍተኛ ጋር ወዳጅ አትሁን፤በቀላሉ ቱግ ከሚልም ሰው ጋር አትወዳጅ፤

25. አለበለዚያ መንገዱን ትማራለህ፤ራስህም ትጠመድበታለህ።

ምሳሌ 22