ምሳሌ 22:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. መልካም ስም ከብዙ ብልጽግና ይመረጣል፤መከበርም ከብርና ከወርቅ ይበልጣል።

2. ባለጠጋና ድኻ የሚጋሩት ነገር፣ እግዚአብሔር የሁላቸውም ፈጣሪ መሆኑ ነው።

3. አስተዋይ ሰው አደጋ ሲያይ መጠጊያ ይሻል፤ብስለት የጐደለው ግን በዚያው ይቀጥላል፤ መከራም ያገኘዋል።

ምሳሌ 22