ምሳሌ 20:18-23 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

18. ምክር ጠይቀህ ዕቅድ አውጣ፤ጦርነት የምትገጥም ከሆነ መመሪያ ተቀበል።

19. ሐሜተኛ ምስጢር ያባክናል፤ስለዚህ ለፍላፊን ሰው አርቀው።

20. አባቱን ወይም እናቱን የሚሰድብ፣መብራቱ በድቅድቅ ጨለማ ይጠፋል።

21. ከጅምሩ ወዲያው የተገኘ ርስት፣በመጨረሻ በረከት አይኖረውም።

22. “ለደረሰብኝ በደል ብድሬን ባልመልስ!” አትበል፤ እግዚአብሔርን ጠብቅ፤ እርሱ ይታደግሃል።

23. ሁለት ዐይነት ሚዛን በእግዚአብሔር ዘንድ አጸያፊ ነው፤ዐባይ ሚዛን አይወደድም።

ምሳሌ 20