ምሳሌ 20:16-22 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

16. ለማይታወቅ ሰው ዋስ የሆነውን ልብሱን ግፈፈው፤ለዘልዛላ ሴት የተዋሰውን በቃሉ ያዘው።

17. ሰው በማጭበርበር ያገኘው ምግብ ይጣፍጠዋል፤በመጨረሻ ግን አፉን ኰረት ሞልቶት ያገኘዋል።

18. ምክር ጠይቀህ ዕቅድ አውጣ፤ጦርነት የምትገጥም ከሆነ መመሪያ ተቀበል።

19. ሐሜተኛ ምስጢር ያባክናል፤ስለዚህ ለፍላፊን ሰው አርቀው።

20. አባቱን ወይም እናቱን የሚሰድብ፣መብራቱ በድቅድቅ ጨለማ ይጠፋል።

21. ከጅምሩ ወዲያው የተገኘ ርስት፣በመጨረሻ በረከት አይኖረውም።

22. “ለደረሰብኝ በደል ብድሬን ባልመልስ!” አትበል፤ እግዚአብሔርን ጠብቅ፤ እርሱ ይታደግሃል።

ምሳሌ 20