ምሳሌ 20:14-17 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

14. ዕቃ የሚገዛ፣ “የማይረባ ነው፤ የማይረባ ነው” ብሎ ያራክሳል፤ሲመለስ ግን በግዢው ይኵራራል።

15. ወርቁም አለ፤ ቀዩም ዕንቊ ተትረፍርፎአል፤ዕውቀት የሚናገሩ ከንፈሮች ግን ብርቅ ጌጦች ናቸው።

16. ለማይታወቅ ሰው ዋስ የሆነውን ልብሱን ግፈፈው፤ለዘልዛላ ሴት የተዋሰውን በቃሉ ያዘው።

17. ሰው በማጭበርበር ያገኘው ምግብ ይጣፍጠዋል፤በመጨረሻ ግን አፉን ኰረት ሞልቶት ያገኘዋል።

ምሳሌ 20