ምሳሌ 20:12-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

12. የሚሰሙ ጆሮዎች፣ የሚያዩ ዐይኖች፣ሁለቱንም እግዚአብሔር ሠርቷቸዋል።

13. እንቅልፍ አትውደድ፤ አለዚያ ድኻ ትሆናለህ፤ዐይንህን ክፈት፤ የተትረፈረፈ ምግብ ይኖርሃል።

14. ዕቃ የሚገዛ፣ “የማይረባ ነው፤ የማይረባ ነው” ብሎ ያራክሳል፤ሲመለስ ግን በግዢው ይኵራራል።

ምሳሌ 20