ምሳሌ 16:27-32 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

27. ወራዳ ሰው ክፋትን ያውጠነጥናል፤ንግግሩም እንደሚለበልብ እሳት ነው።

28. ጠማማ ሰው ጠብን ይዘራል፤ሐሜተኛም የቅርብ ወዳጆችን ይለያያል።

29. ክፉ ሰው ባልንጀራውን ያባብለዋል፤መልካም ወዳልሆነውም መንገድ ይመራዋል።

30. በዐይኑ የሚጠቅስ ሰው ጠማማነትን ያውጠነጥናል፤በከንፈሩ የሚያሽሟጥጥም ወደ ክፋት ያዘነብላል።

31. ሽበት የክብር ዘውድ ነው፤የሚገኘውም በጽድቅ ሕይወት ነው።

32. ታጋሽ ሰው ከጦረኛ፣ስሜቱን የሚገዛም ከተማን በጒልበቱ ከሚይዝ ይበልጣል።

ምሳሌ 16