ምሳሌ 16:18-22 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

18. ትዕቢት ጥፋትን፣የእብሪት መንፈስም ውድቀትን ትቀድማለች።

19. በተዋረደ መንፈስ ከተጨቈኑት ጋር መሆን፣ከትዕቢተኞች ጋር ብዝበዛን ከመካፈል ይሻላል።

20. ምክርን የሚሰማ ይለመልማል፤ በእግዚአብሔርም የሚታመን ቡሩክ ነው።

21. ልባቸው ጠቢብ የሆነ አስተዋዮች ይባላሉ፤ደስ የሚያሰኙ ቃላትም ዕውቀትን ያዳብራሉ።

22. ማስተዋልን ገንዘብ ላደረጋት የሕይወት ምንጭ ናት፤ቂልነት ግን በተላሎች ላይ ቅጣት ታመጣባቸዋለች።

ምሳሌ 16