ምሳሌ 16:17-21 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

17. የቅኖች ጐዳና ከክፋት የራቀ ነው፤መንገዱንም የሚጠብቅ ሕይወቱን ይጠብቃል።

18. ትዕቢት ጥፋትን፣የእብሪት መንፈስም ውድቀትን ትቀድማለች።

19. በተዋረደ መንፈስ ከተጨቈኑት ጋር መሆን፣ከትዕቢተኞች ጋር ብዝበዛን ከመካፈል ይሻላል።

20. ምክርን የሚሰማ ይለመልማል፤ በእግዚአብሔርም የሚታመን ቡሩክ ነው።

21. ልባቸው ጠቢብ የሆነ አስተዋዮች ይባላሉ፤ደስ የሚያሰኙ ቃላትም ዕውቀትን ያዳብራሉ።

ምሳሌ 16