ምሳሌ 14:13-16 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

13. በሣቅ ጊዜ እንኳ ልብ ይተክዛል፤ደስታም በሐዘን ሊፈጸም ይችላል።

14. ልባቸውን ከጽድቅ የሚመልሱ የእጃቸውን ሙሉ ዋጋ ይቀበላሉ፤ደግ ሰውም ወሮታውን ያገኛል።

15. ተላላ ሰው ሁሉን ያምናል፤አስተዋይ ግን ርምጃውን ያስተውላል።

16. ጠቢብ ሰው ጥንቁቅ ነው፤ ከክፉም ይርቃል፤ተላላ ግን ችኵልና ደንታ ቢስ ነው።

ምሳሌ 14