ምሳሌ 10:28-31 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

28. የጻድቃን አለኝታ ደስታ ነው፤የክፉዎች ተስፋ ግን ከንቱ ሆኖ ይቀራል።

29. የእግዚአብሔር መንገድ ለጻድቃን መጠጊያ፣ክፉ ለሚያደርጉ ግን መጥፊያቸው ነው።

30. ጻድቃን ፈጽሞ አይነቀሉም፤ክፉዎች ግን በምድር አይኖሩም።

31. የጻድቃን አንደበት ጥበብን ያፈልቃል፤ጠማማ ምላስ ግን ትቈረጣለች።

ምሳሌ 10