ምሳሌ 10:2-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

2. ያላግባብ የተገኘ ሀብት አይጠቅምም፤ጽድቅ ግን ከሞት ይታደጋል።

3. እግዚአብሔር ጻድቁ እንዲራብ አያደርግም፤የክፉዎችን ምኞት ግን ያጨናግፋል።

4. ሰነፍ እጆች ሰውን ያደኸያሉ፤ትጉ እጆች ግን ብልጽግናን ያመጣሉ።

5. ሰብሉን በበጋ የሚሰበስብ ጠቢብ ልጅ ነው፤በመከር ጊዜ የሚተኛ ግን ውርደት ይከተለዋል።

6. በረከት በጻድቃን ራስ ላይ ነው፤መዓት ግን የክፉዎችን አፍ ይዘጋል።

7. የጻድቃን መታሰቢያቸው በረከት ነው፤የክፉዎች ስም ግን እንደ ጠፋ ይቀራል።

ምሳሌ 10