43. እርሱም እንዲህ አላቸው፤ “ታዲያ፣ ዳዊት በመንፈስ ቅዱስ ኀይል ለምን ‘ጌታዬ’ ይለዋል? ለምንስ፣ እንዲህ ይለዋል?
44. “ ‘እግዚአብሔር ጌታዬን፤ ጠላቶችህን ከእግርህ በታች እስካንበረክ ክልህ ድረስ፣ በቀኜ ተቀመጥ።” ’
45. ስለዚህ ዳዊት፣ ‘ጌታዬ’ ብሎ ከጠራው፣ እንዴት ልጁ ሊሆን ይችላል?”
46. አንድ ቃል ሊመልስለት የቻለ ወይም ከዚያን ቀን ጀምሮ ሊጠይቀው የደፈረ ማንም አልነበረም።