ማቴዎስ 22:41-44 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

41. ፈሪሳውያን ተሰብስበው ሳሉ ኢየሱስ፣ እንዲህ ሲል ጠየቃቸው፤

42. “ስለ ክርስቶስ ምን ይመስላችኋል? የማንስ ልጅ ነው?”እነርሱም፣ “የዳዊት ልጅ ነው” አሉት።

43. እርሱም እንዲህ አላቸው፤ “ታዲያ፣ ዳዊት በመንፈስ ቅዱስ ኀይል ለምን ‘ጌታዬ’ ይለዋል? ለምንስ፣ እንዲህ ይለዋል?

44. “ ‘እግዚአብሔር ጌታዬን፤ ጠላቶችህን ከእግርህ በታች እስካንበረክ ክልህ ድረስ፣ በቀኜ ተቀመጥ።” ’

ማቴዎስ 22